********************************************
ዛሬ ህዳር 13/2014 ዓ.ም:- "#ደማችን_ለመከላከያ_ሰራዊታችን" መርሐ-ግብር አጠቃላይ የኮሌጁ ሰልጣኞች፣ አሰልጣኞች እና አስተዳደር ሰራተኞች አሳትፎ ተከናውኗል። በመርሀ ግብሩ የተሳተፉ አካላትም በሰጡት አስተያየት መርሐ-ግብሩ በመዘጋጀቱ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው የሀገራችንን ሉዓላዊነት ለማስከበር ግንባር ላይ ህይወቱን እየሰጠ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊታችን ከዚህም በላይ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንና በቀጣይም በተለያዩ መንገዶች ድጋፋቸውን ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸው ገልጸዋል።
0 Comments