የክልሉ የቴ/ሙ/ት/ስ/ቢሮና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች በኮሌጃችን የስራ ጉብኝት አደረጉ፡፡

*******************************************
ህዳር 09/2014 ዓ.ም: የክልሉ የቴ/ሙ/ት/ስ/ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር እንዳልካቸው ጌታቸው ጨምሮ የቢሮው ምክትል ኃላፊዎችና የማኔጅመንት አካላት እንዲሁም የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች ያሳተፈ የልዑካን ቡድን በኮሌጃችን በመገኘት ጉብኝት አደረጉ። ጓብኚዎቹ ኮሌጃችን በወቅታዊ ጉዳይ ላይ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴና የተግባር አፈጻጸማችንን ማየት ችለዋል፡፡በተጨማሪም የግንባታ ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ የኮሌጁ አስተዳደር ህንፃ ለረጅም ጊዜ የተጓተተ፣ በተሰጠው ውል መሰረት ያልተጠናቀቀ በመሆኑ እየገጠመን ስላለው ችግር ገለፃ ተደርጎላቸዋል። የግብኝቱ ዋና አላማን በተመለከተ ከትውውቅ ባሻገር የኮሌጃችንን እንቅስቃሴ ደረጃ ለማየትና በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ በሚሰራባቸው ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ለማግኘት ታሳቢ ያደረገ መሆኑ የቢሮ ኃላፊ ተናግረዋል፡፡